የ ጠበል መድሃኒትን በጎልዓ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ዮሃንስ(ዓዲግራት)
No Thumbnail Available
Date
2025-06-25
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Mekelle University
Abstract
ይህ ጥናት “የጠበል መድሃኒትነት በጎልዓ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ዮሃንስ”(ዓዲግራት) በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን ጥናቱም በሃገረሰባዊ ልማድ ስር እንደሚካተት በሚገለጸው ሃይማኖታዊ ፎክሎር ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የጥናቱ ማእከላዊ ጉዳይ ግን በእምነተና እምነታዊ ድርጊት ላይ ይሆናል። ይህንን ማእከላዊ ሃሳብ ኣጉልተው ሊያሳዩ ከመረጃ ኣቀባዮች በቃለ መጠየቅ የተገኘ ሃሳብ ያሳያል።
በተጨማሪም በምርምሩ ውስጥ ኣምስት ምእራፎች የያዘ ሲሆን እነሱም በምእራፍ ኣንድ ላይ የጥናቱ ዳራ ፣ የጥናቱ ኣነሳሽ ምክንያት፣ የጥናቱ ኣላማ፣ የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ ኣስፈላጊነት፣የጥናቱ ዘዴ፣ የመረጃ ኣሰባሰብ ዘዴ፣ የጥናቱ ኣደረጃጀት፣ የጥናቱ የመረጃ ምንጮች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እና የመስክ ተሞክሮ ሲሆኑ፣ በምእራፍ ሁለት ደግሞ ክለሳ ድርሳናትና የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት ማግኘት ስላልተቻለ ኣልተካተተበትም ቀጥሎም፣ በምእራፍ ሶስት የምናገኘው ኣጠቃላይ ጥናቱን የተጠቀመበትን ዘዴ ኣካትተዋል፣ በምእራፍ ኣራት ደግሞ ጥናቱን ሙሉ ትንታኔ ኣካትቶ የያዘ ሲሆን፣ በምእርእፍ ኣምስትና በመጨረሻው ምእራፍ የሆነው ማጠቃለያን በውስጡ ኣካቶ ይዘዋል በመሆኑም የጥናቱ ትኩረት የሆነው ጠበልን በፈዋሽነታቸው በስርኣታቸው በኣመሰራረታቸው እምነትና እምነታዊ ድርጊት ኣምነው ለመጡ ተጠማቂዎች ያለውን ኣገልግሎት ለማሳየት ጥረት ተደርገዋል በጥናቱ ከተለያዩ ኣብያተ መጽሃፍት የሚገኙ መረጃዎችን ከመሰብሰብ ጀምሮ ስለ ጠበልና የኣከዋወን ስራቶችን በቃለ መጠይቅ፣ በምልከታ መረጃ ለመሰብሰብ ተሞክረዋል።
መረጃዎችም በመቅርጸ ድምጽ፣ በፎቶና በቪድዮ ካሜራ እንዲሁም በእጅ ማስታዎሻ ተይዘዋል። የመስክ መረጃ ሰጪዎች ከክርስትና እምነት ተከታዮች እና ከእስልምና እምነት ተከታዮች የተውጣጡ ሲሆኑ ከእምነት መድሃኒት ተጠቃሚዎች፣ ከሀገር ሽማግላዎች፤በአሊማ ተኮር፣ አመቺ እና ጠቋሚ የናሙና አመራረጥ ስሌት ተመርጠዋል፡፡ ከቁልፍ እና ከአጋዥ መረጃ አቀባዮች የተሰበሰቡ መረጃዎች አይነታዊ የምርምር ስሌት በመጠቀም በይዘትና በምድብ ተደራጅተዋል፡፡
አነሳሽ ምክንያት ደግሞ የጠበልን መድሃኒትነት (ፈዋሽነት) መመርመር ነው፡፡ የምርምሩ ዋና አላማ የማህበረሰቡን ሀገረሰባዊ ልማድ እውቀት፣ ፈዋሽነትን በመመርመር ባህላዊ ልማደን ገልጾ ማሳየት ሲሆን በአካባቢው በእምነት ህክምና (ጠበል) የሚፈወሱ በሽታዎችን ማየት፣ ጠበል ቦታ ከመሄዳችን በፊት ማድረግ ያለብን ንነገሮች ምን መሆን እንዳለባቸው ማሳየት የሚል ዝርዝር አላማዎች አሉት፡፡
በትንታኔው መሰረት ለጥናት የተመረጠው ሁለት የጠበል ቦታዎች ላይ በአብዛኛው የአካባቢውን ማህበረሰብ የተፈወሱትን በሽታዎችም ቁስል፣ የሚጥል በሽታ፣ አልማዝ ባለጭራ፣ የኣእምሮ በሽታ፣ ሴቶች ላይ ኣላስፈላጊ ደም መፍሰስ፣ ኣካላት የመልመስ በሽታ፣የኩላሊት በሽታ፣ ካንሰር፣ኢችኣይቪ፣ኪንታሮት፣ወዘተ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
