የማዳመጥ ክሂል ተግባራትና ክንዉኖች የተማሪዎ ቹ የማዳመጥ ክሂል ለማዳበር ያላቸዉ ተገቢነት ፍተሻ (በ10ኛ ክፍል መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት)

dc.contributor.authorልእልቲ ንጉስ ወልደሃ ና
dc.date.accessioned2026-04-26T06:01:14Z
dc.date.issued2025-10-25
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በ10ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መማርያ መፅሐፍና መርሃ ትምህርት ውስጥ የተካተቱ የማዳመጥ ክሂል ተግባራትና ክንውኖች የተማሪዎችን የማዳመጥ ክሂል ለማዳበር ያላቸው ተገቢነት መፈተሽ ነበር፡፡ ይህ ጥናት ገላጭዳሰሳ (descriptive survey) የምርምር ንድፍን የተከተለ ሲሆን መጠናዊ (quantitative) እና ዓይነታዊ (qualitative) የምርምር ዘዴዎችን በመጠቀም በ2015 ዓ.ም በታተመው የ10ኛክፍል የአማርኛ መማሪያ መፅሐፍና የማዳመጥ ትምህርት ይዘቶች ለይቶ በማውጣት የቀረቡት ተግባራትና ክንውኖችው የተማሪዎችክሂል ከማዳበር አኳያ ያላቸውን ብቃትመፈተሽ ነበር። በመጀመሪያ አጥኚዋ በመማሪያ መፅሐፉ ላይ ከተለያዩ ሙሁራን የመገምገሚያ ማዕቀፎች (Frameworks) አውጥታ በመፅሐፉ የሰነድ ፍተሻ (document analysis) አካሂዳለች፡፡ በመቀጠል ደግሞ የማዳመጥ ክሂል ተግባራትና ክንውኖች ጋር በተያያዘ ከአማርኛ መምህራን በተደረገ የቡድን ውይይት መንገድ (Focus Group Discussion) የተገኙ መረጃዎች ተተንትነው ቀርቧል፡፡ ከዚያም የማዳመጥ ክሂል ተግባራት ክንውኖች የተማሪዎቹን ክሂል ለማዳበር ያላቸውን ተገቢነት በተመለከተ በማይጨው ከተማ ካሉት ሥስት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል እንደናሙና በተወሰዱት ስድስት የ10ኛ ክፍል አማርኛ መምህራን የፅሑፍ መጠይቅ በማሰራጨት የተገኘው መረጃ ተተንትኖ ቀርቧል። በመጨረሻ የ10ኛ ክፍል አማርኛ መምህን ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 5 መምህራን በቡድን ውይይት መንገድ መፅሓፉ የተካተቱት የማዳመጥ ክሂል ተግባራት ክንውኖች ጠንካራና ደካማ ጎኖችን የገመገሙ ሲሆን߹ የተገመገሙት ነጥቦች ደግሞ ተተንትኖው ቀርቧል። በዚህ መሰረትም አጥኚዋ ባደረገችው የሰነድ ፍተሻና በፅሑፍ መጠይቅ በመማሪያ መፅሓፉ ያሉት የማዳመጥ ክሂል ተግባራትና ክንውኖች የተማሪዎቹን የማዳመጥ ክሂል በማዳበር ያለቸው ተገቢነት መልካም እንደሆነ ነው ።ይኸውም መልከም እንደሆነ ነው። ምክንያቱም በአብዛኞቹ ምዕራፎች የቀረቡት የማዳመጥ ክሂል ተግባራት ክንውኖች የተማሪዎቹን ፍላጎት ߹ የክፍል ደረጃ ߹ ዕድሜ ባህላዊ ዳራና መስህብነት በተመለከተ ከነበረው መፅሓፍ ብተሻለ መንገድ የቀረበ መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል። ከዚያም በተጨማሪ ከመምህራን ፅሑፋዊ መጠይቅ የተገኘው መረጃም እንደሚያመልክተው በ10ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መፅሓፍ ውስጥ ያሉት የማዳመጥ ክሂል ተግባራት ክንውኖች መምህራን አልፎ አልፎ እስማማሎህ የሚል ነው። ከዚህ የተነሳ እንደ አጥኚዋ ድምዳሜ በ10ኛ ክፍል አማርኛ መማሪያ መፅሓፍ የተካተቱት የማዳመጥ ክሂል ተግባራት ክንውኖች መማሪያ በአብዛኞቹ ተማሪዎቹን ክሂል ለማዳበር ተገቢነት ያላቸው እንኳ ቢሆኑ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች ዳግሞ በሁሉም ምዕራፎች በንግግርና ንባብ መልክ የቀረቡ በመሆናቸው ከዚህ ወጣ ባለ መልኩ ብቀርቡ ይሻል እንደነበር ነው። ይኸውም ከሚደመጡ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተያያዥነት ያላቸው ስዕላዊ መገለጫዎችና በካሴት ወይም በሬድዮ የተቀረፁ ድምፆችን ወደ ክፍል ይዞ በመግባት የተማሪዎችን የማዳመጥ ክሂል ለበለጠ ለማዳባር ተገቢነት ይኖረው ነበር። በመጨረሻም በሥስቱም የምርምር መተንተኛ ዘዴዎች አማኝነት የተገኘው መረጃና የውጤት ማብራሪያ መሠረት ተገቢ መደምደሚያና አስተያየት ተሰጥቷል።
dc.identifier.urihttps://repository.mu.edu.et/handle/123456789/1368
dc.language.isoen
dc.publisherMekelle University
dc.titleየማዳመጥ ክሂል ተግባራትና ክንዉኖች የተማሪዎ ቹ የማዳመጥ ክሂል ለማዳበር ያላቸዉ ተገቢነት ፍተሻ (በ10ኛ ክፍል መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
Lielti Nigus weldehana.pdf
Size:
1.31 MB
Format:
Adobe Portable Document Format

License bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: