Repository logo

ሥነጽሑፋዊ ቅንጫቢዎች የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ለማስተማር ያላቸው ተገቢነት በ4ኛ እና 5ኛ ክፍል በትግርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ናሙናነት

dc.contributor.authorሙሉጌታ ይብራህ
dc.date.accessioned2026-04-26T06:38:17Z
dc.date.issued2025-10-25
dc.description.abstractይህ ጥናት ሥነጽሑፋዊ ቅንጫቢዎች የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ለማስተማር ያላቸው ተገቢነት በ4ኛ እና 5ኛ ክፍል በትግርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ናሙናነት በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የ4ኛ እና 5ኛ ክፍል የትግርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የተካተቱ ሥነጽሁፋዊ ቅንጫቢዎች የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ለማስተማር ያላቸው ተገቢነት መመርመር ነው። በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ መማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ የተካተቱትን ሥነጽሁፋዊ ቅንጫቢዎች የማንበብ ክሂልንና የማዳመጥ ክሂልን ለማስተማር የተደራጁበት መንገድ ተገቢነውን? በተተኳሪ መጻህፍቱ ያላቸውስ ሽፋን ምን ይመስላል? ተማሪዎች የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ተግባራዊ ልምምድ እንዲያካሂዱ በሚያስችል መልኩ ተደራጅተዋልን? ሥነጽሁፋዊ ቅንጫቢዎቹ የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ለማስተማር ተስማሚ ናቸዉን? የሚሉ መስረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። የዚህ ጥናት ዓላማ ለማሳካት ገላጭ የምርምር ንድፍ የተመረጠ ሲሆን፣ የተገኙ መረጃዎች አይነታዊ የምርምር አቀራረብ ዘዴን ተከትሎ ተተንትነዋል። በጥናቱ ሰነድ ፍተሻ ጥቅም ላይ የዋለ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ነው። ጥናቱን ለማካሄድ በተተኳሪዎቹ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የተካተቱ የስነጽሁፍ ቅንጫቢዎች ለይቶ በማዉጣት በክለሳ ድርሳናት የተካተቱትን የበድሉ (1996) ፣ lazar (2003) እና ሌሎችም የሚያራምዷቸውን ንድፈ ሀሳባዊ መሰረቶችን በመመርኮዝ ትንተና ተሰጥቶባቸዋል። በጥናቱ የተገኘውን ውጤት እንደሚያመለክተው በተተኳሪ መጻህፍቱ የተካተቱ የስነ ጽሁፍ ቅንጫቢዎች ከኢ-ስነ ጽሁፋዊ ጽሁፎች አንጻር ስንመዝናቸው እጅጉን ያነሱ ናቸው።
dc.identifier.urihttps://repository.mu.edu.et/handle/123456789/1370
dc.language.isoen
dc.publisherMekelle University
dc.titleሥነጽሑፋዊ ቅንጫቢዎች የማዳመጥና የንባብ ክሂሎችን ለማስተማር ያላቸው ተገቢነት በ4ኛ እና 5ኛ ክፍል በትግርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ናሙናነት
dc.typeThesis

Files

Original bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
mulugeta yibrah.pdf
Size:
891.81 KB
Format:
Adobe Portable Document Format

License bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: