በ2015ዓ.ም የተዘጋጀው የ9ኛ ክፍል የኣማርኛ ቋንቋ የተማሪው መፅሃፍ እና የመርሃ ትምርቱ ተዛምዶ ፍተሻ
| dc.contributor.author | ወይንሸት ኣማረ | |
| dc.date.accessioned | 2026-04-26T07:02:19Z | |
| dc.date.issued | 2025-11-25 | |
| dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በ2015 ዓ.ም የተዘጋጀው የ9ኛ ክፍል የኣማርኛ ቋንቋ የተማሪ መፅሃፍ ከ9ኛ ክፍል የኣማርኛ ቋንቋ መርሃ ትምህርት (Syllabus) ጋር ያለውን ተዛምዶ (Alignment) መፈተሽ ነው። ይህንን ዓላማ ለማሳካት ጥናቱ የተቀላቀለ የምርምር ዘዴን (Mixed-methods) እና ገላጭ የምርምር ንድፍን ተጠቅሟል። የጥናቱ መረጃዎች የተሰበሰቡት የሰነድ ፍተሻ ዘዴን በመጠቀም ሲሆን፣ የመማሪያ መፅሃፉን እና መርሃ ትምህርቱን ለመተንተን የይዘት ትንተና ማረጋገጫ ዝርዝር (Checklist) እና የይዘት ትንተና ሩብሪክ (Rubric) በዋና የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያነት ኣገልግለዋል። የተሰበሰቡት መረጃዎችም በመጠናዊ እና ኣይነታዊ የትንተና ዘዴዎች ተተንትነዋል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያመለክተው፣ በመርሃ ትምህርቱ የተቀመጡ ኣብዛኛዎቹ የመማር ውጤቶች፣ በተለይም የማዳመጥ፣ የማንበብ፣ የመፃፍ እና የሰዋስው ይዘቶች በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ (እስከ 100%) ተሸፍነዋል። ይሁን እንጂ፣ የመናገር ክህሎት (50%) እና የስነፅሁፍ ይዘት (20%) ሽፋን ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር ኣነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል። በዘዴ ኣጠቃቀም ረገድ፣ መርሃ ትምህርቱ ተማሪን ያማከለ እና የቡድን ስራን የሚያበረታታ ኣቅጣጫ ቢኖረውም፣ በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ የተካተቱት ተግባራት ግን በኣብዛኛው በግል የሚሰሩና ድግግሞሽ የሚታይባቸው ሆነው ቀርበዋል። በተጨማሪም የቃላት እና የሰዋስው ይዘቶች በስፋት ቢቀርቡም፣ በቂ የሆነ ፅንሰሃሳባዊ ማብራሪያ የጎደላቸው መሆኑ ተረጋግጧል። በጥቅሉ፣ የመማሪያ መፅሃፉ ከመርሃ ትምህርቱ ጋር በዋና ዋና የቋንቋ ክህሎቶች ረገድ ጠንካራ ተዛምዶ እንዳለው፣ ነገር ግን በተግባቦታዊ ክህሎት ልምምድ፣ በስነፅሁፍ ይዘት ሽፋን እና በተግባራት ኣቀራረብ ላይ ክፍተቶች እንዳሉበት ተደምድሟል። በመጨረሻም፣ በቀጣይ የመፅሃፍ ማሻሻያዎች ላይ የመናገር እና የስነፅሁፍ ይዘቶች ትኩረት እንዲሰጣቸው፣ ተግባራት በቡድን እና በተግባቦት ላይ ያተኮሩ ሆነው እንዲዘጋጁ እና ለሰዋስው ይዘቶች በቂ ማብራሪያ እንዲካተት የጥናቱ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። | |
| dc.identifier.uri | https://repository.mu.edu.et/handle/123456789/1372 | |
| dc.language.iso | other | |
| dc.publisher | Mekelle University | |
| dc.title | በ2015ዓ.ም የተዘጋጀው የ9ኛ ክፍል የኣማርኛ ቋንቋ የተማሪው መፅሃፍ እና የመርሃ ትምርቱ ተዛምዶ ፍተሻ | |
| dc.type | Thesis |