በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ደጋግሞ የማንበብ ብልሃት አቀላጥፎ ማንበብን ለማዳበር ያለው አስተዋፅኦ (በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

dc.contributor.authorመሓሪት ገ/ፃዲቕ
dc.date.accessioned2026-04-26T06:30:50Z
dc.date.issued2025-10-25
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ደጋግሞ የማንበብ ብልሃት (Repeated Reading Strategy) በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ አቀላጥፎ የማንበብ ክህሎት ላይ ያለውን ተፅዕኖ መመርመር ነበር። ጥናቱ ትኩረት ያደረገው የደጋግሞ ማንበብ ስልት በተማሪዎች የንባብ ፍጥነት፣ ትክክለኛነት እና ስሜት ገላጭ አነባበብ (Prosody) ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በመፈተሽ ላይ ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ጥናቱ ፍትነት-መሰል (Quasi-experimental) የሆነ፣ ማለትም አቻ ያልሆነ የቁጥጥር ቡድን የቅድመ እና ድህረ-ሙከራ ንድፍን ተከትሎ ተካሂዷል። የጥናቱ ተሳታፊዎች በትግራይ ክልል በአላማ ከተመረጠ አንድ የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ 80 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ፣ በሁለት ቡድን (40 የሙከራ እና 40 የቁጥጥር ቡድን) ተከፍለው በጥናቱ ተሳትፈዋል። ለሙከራ ቡድኑ ለስምንት ሳምንታት ያህል የደጋግሞ ማንበብ ጣልቃገብነት ትግበራ ሲደረግ፣ የቁጥጥር ቡድኑ ግን መደበኛ ትምህርቱን ቀጥሏል። መረጃዎች የተሰበሰቡት ደረጃቸውን የጠበቁ የአቀላጥፎ ማንበብ መለኪያ ፈተናዎችን በመጠቀም ሲሆን፣ የተሰበሰበው መረጃም የጋራ ተለዋዋጭ ትንተና (ANCOVA) ስታቲስቲክስን በመጠቀም ተተንትኗል። የጥናቱ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት፣ ጣልቃገብነቱ ከመሰጠቱ በፊት በሁለቱም ቡድኖች መካከል ጉልህ ልዩነት አልነበረም። ነገር ግን ከስልጠናው በኋላ የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ጋር ሲነፃፀሩ በንባብ ፍጥነት (በደቂቃ በትክክል የተነበቡ ቃላት)፣ በንባብ ትክክለኛነት እና በስሜት ገላጭ አነባበብ ከፍተኛ እና በስታቲስቲክስ ጉልህ የሆነ (p < 0.05) መሻሻል አሳይተዋል። የANCOVA ውጤትም የቅድመ-ሙከራ ውጤቶችን ተፅዕኖ ከተቆጣጠረ በኋላም ቢሆን ልዩነቱ የጎላ መሆኑን አረጋግጧል። ከዚህ በመነሳት፣ ደጋግሞ የማንበብ ብልሃት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን የአማርኛ አቀላጥፎ የማንበብ ችግር ለመቅረፍ ውጤታማ ዘዴ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። በመሆኑም የቋንቋ መምህራን ይህንን ስልት በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በስፋት ቢጠቀሙበት፣ እንዲሁም የስርዓተ ትምህርት አዘጋጆች ለአቀላጥፎ ማንበብ የሚሆኑ አጫጭር ምንባቦችን በመፅሀፍት ውስጥ ቢያካትቱ የተሻለ የንባብ ክህሎትን ማዳበር እንደሚቻል ምክረሀሳብ ቀርቧል።
dc.identifier.urihttps://repository.mu.edu.et/handle/123456789/1369
dc.language.isoen
dc.publisherMekelle University
dc.titleበአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ደጋግሞ የማንበብ ብልሃት አቀላጥፎ ማንበብን ለማዳበር ያለው አስተዋፅኦ (በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
Meharit gebretsadik Gebru.pdf
Size:
1.11 MB
Format:
Adobe Portable Document Format

License bundle

Now showing 1 - 1 of 1
Loading...
Thumbnail Image
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: