በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የትግርኛ መማርያ መጽሐፎች የክሂሎች ዓምዳዊ አደረጃጀት ግምገማ” (ከተሻሻለው የብሉም ታክሶኖሚ 2001 ስርጭት እይታ አንፃር)
| dc.contributor.author | ተስፋይ ካሕሳይ | |
| dc.date.accessioned | 2026-04-26T07:29:31Z | |
| dc.date.issued | 2025-10-25 | |
| dc.description.abstract | ይህ ጥናት በ2008 ዓ.ም. በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የታተሙና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመደበኛ ትምህርት ቤቶች እና በርቀት ትምህርትቤቶች ስራ ላይ የዋሉ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የትግርኛ የተማሪ መማሪያ መፃሕፍት ውስጥ ያሉ የቋንቋ ክህሎት ተግባራት ዓምዳዊ አደረጃጀት (vertical alignment) ከተሻሻለው የብሉም ታክሶኖሚ (Revised Bloom’s Taxonomy – RBT, Anderson & Krathwohl,2001) እይታ አንፃር መገምገም ዋና ዓላማ አድርጎ ወስዷል። የጥናቱ ስልት ተጋናኝ ትይዩ ቅይጥ ዘዴ (convergent parallel mixed-methods design) ተጠቅሟል። በመር የይዘት ትንተና (directed content analysis) በጠቅላላ 779 ተግባራት (9ኛክፍል 407፣ 10ኛ ክፍል 372) በ Anderson & Krathwohl (2001) መሰረት ተመድበው ተተንትነዋል፤ በተጨማሪም በዓላማ ተኮር ናሙና ዘዴ የተመረጡ ከመፃሕፍቱ ዋና አዘጋጅ (1) እና ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ካላቸው የሁለተኛ ድግሪ ትግርኛ ቋንቋ መምህራን (3) ጋር ከፊል-የተዋቀረ ቃለ መጠይቅ ተካሂዷል። ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት በሁለቱም ክፍሎች ከጠቅላላ ተግባራት ዝቅተኛ የማሰብ ክህሎት (LOTS) 90.37% (~90) ሲሆን፤ ከፍተኛ የማሰብ ክህሎት ደግሞ (HOTS) 9.63% (~10) ይህም ማለት በ9ኛ ክፍል 11.06% እና በ10ኛ ክፍል 8.06% ማለት ነው። ስለሆነም ከ9ኛ ወደ 10ኛ ክፍል HOTS በ3% (regression in cognitive progression) ቀንሷል። እንዲሁም በማንበብ እና በማዳመጥ ክሂሎች ውስጥ በ10ኛ ክፍል HOTS በቅደም ተከተል ከ3% እና 5% ወደ 0% ወርዷል። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት ክሂሎቹ በዚህ የክፍል ደረጃ በተከታታይነት ባለመቅረባቸው መሆኑ አጥኚው አረጋግጧል። በምዕራፎች ውስጥ እና በክፍሎቹ መካከል ተከታታይነት እና ተለጣጣቂነት በከፍተኛ ደረጃ አልተመጣጠነም። የቃለ መጠይቅ ውጤቶችም ይህን አረጋግጠዋል፤ መፃሕፍቱ ተገቢና ግልጽ የሆነ ሞዴል አለመጠቀማቸው፣ የአንድን መጽሐፍ ምዕራፎች በግለሰብ ደረጃ ተከፋፍለው መዘጋጀታቸው ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት እንዳይኖራቸው አድርገዋል። ጥናቱ መፃሕፍት በቡድን እና በRBT መሰረት እንዲዘጋጁ፣ የመፃሕፍት አዘጋጆችና መምህራን ቀጣይነት ያለው ስልጠና እንዲያገኙ፣ ከፍተኛ የማሰብ ክህሎት የሚያዳብሩ ተግባራት እንዲጨመሩ ይመከራል። | |
| dc.identifier.uri | https://repository.mu.edu.et/handle/123456789/1375 | |
| dc.language.iso | other | |
| dc.publisher | Mekelle University | |
| dc.title | በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የትግርኛ መማርያ መጽሐፎች የክሂሎች ዓምዳዊ አደረጃጀት ግምገማ” (ከተሻሻለው የብሉም ታክሶኖሚ 2001 ስርጭት እይታ አንፃር) | |
| dc.type | Thesis |